የእሳትና መብረቅ ዋስትና (Fire& Lightening Insurance)

ይህ ውል በእሳት ቃጠሎ፣ በመብረቅ አደጋና ለቤት ውስጥ አገልግሎት ብቻ በሚውል ማሞቂያ ወይም ቦይለር በሚደርስ ፍንዳታ ምክንያት በንብረት ላይ ለሚደርስ ጉዳት የመድን ሽፋን ይሰጣል፡፡ በዚህ የዋስና ሽፋን ከለላ የሚያገኙት በአንድ በተወሰነ ቦታ የሚገኙ የሚንቀሳቀሱም ይሁን የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ሲሆኑ ውሉ በሁለት አማራጭ ይሰጣል፡፡ እነዚህም፡ -

 • መሰረታዊ ሽፋን እና
 • መሰረታዊ ሽፋን ከተጨማሪ አደጋዎች ጋር

ውል ለመግባ የሚያስፈልጉ ነገሮች

 • የንብረቶች እና የዕቃዎች ዝርዝር ከነዓይነትና ዋጋቸው
 • ለህንፃዎችና ለመኖሪያ ቤቶች የባለቤትነት ማረጋገጫ/ካርታ
 • ከዚህ በተጨማሪ ደንበኛው ስለንብረቱ እውነተኛና በቂ መረጃ ለድርጅቱ መስጠት ይኖርበታል፡፡

በመሰረታዊ ውል የማይሸፈኑ ክስተቶች

 • በንብረቱ የተፈጥሮ ባህሪ የተነሳ የሚመጣ መቀጣጠልና እሳት
 • ማንኛውም ዓይነት ዝርፊያ (ከቃጠሎ ጋር ቢያያዝም ባይያያዝም)
 • በተፈቀደለት የመንግስት አካል ትዕዛዝ መሰረት የሚደርስ ቃጠሎ
 • ከመሬት ውስጥ በመነጨ እሳት ምክንያት የሚመጣ ቃጠሎ
 • ከላይ ውሉ ይሸፍነዋል ተብሎ ከተጠቀሰው ውጭ ያለ ፍንዳታ
 • ከጫካ፣ ከቁጥቋጦና መሰል ነገሮች በሚነሳ እሳት የሚመጣ አደጋ
 • በመሬት መንቀጥቀጥ፣ በእሳተ ገሞራ እና በተመሳሳይ የተፈጥሮ ክስተቶች የሚነሳ የእሳት አደጋ
 • በጦርነትና መሰል ነገሮች የሚነሳ የእሳት አደጋ
 • አደጋው ከመከሰቱ በፊት ወይም በአደጋው ጊዜ የባህር ላይ ጉዞ (ማሪን) መድን በተገባለት ንብረት ላይ ለሚደርስ የእሳት ቃጠሎ

ተጨማሪ የሽፋን ዓይነቶች 

በደንበኛው ፍላጎት ተጨማሪ አረቦን ተከፍሎ ከሚካተቱ የአደጋ ዓይነቶች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡

 • አውሎ ነፋስና የባህር ሞገድ
 • በውኃ መጥለቅለቅ
 • በውኃ ቧንቧዎች ፍንዳታ
 • በሦስተኛ ወገን ሆን ተብሎ በሚደርስ አደጋ
 • በከብቶች ወይም በተሽከርካሪዎች በሚደርስ ግጭት
 • የመሬት መንቀጥቀጥ
 • የአውሮፕላን አደጋ
 • በህዝባዊ አመፅ
 • በፍንዳታ
 • በሰደድ እሳት
 • በመሬት መደርመስ እና በመሳሰሉት፡፡

የካሳ ክፍያን በተመለከተ

 • ድርጅቱ ጉዳት የደረሰበትን ንብረት ከአደጋው በፊት ወደነበረበት ቦታ የመመለስ፣ ከአደጋው በፊት ያለውን ዋጋ የመስጠት፣ ወይንም ንብረቱን በተመሳሳይ መልኩ የመተካት አማራጭ ይኖረዋል፡፡
 • በአደጋው ጊዜ የንብረቱ ዋጋ መድን ከተገባለት ዋጋ ከበለጠ ደንበኛው ለልዩነቱ ኃላፊነቱን የሚወስድ ሲሆን የድርጅቱ የኃላፊነት መጠንም ይህንኑ ባገናዘበ መልኩ በተመጣጣኝ ሁኔታ በንፅፅር የሚሰላ ይሆናል፡፡ ይህም በእያንዳንዱ ንብረት ላይ በተናጠል ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

በአደጋ ጊዜ መደረግ የሚገባቸው ሁኔታዎች

 • ደንበኛው ስለአደጋው ለድርጅቱ በፍጥነት በፅሑፍ ያሳውቃል
 • ደንበኛው በሚቻለው አቅም አደጋውን ለመቀነስ ተገቢውን እርምጃ ይወስዳል ተብሎ ይጠበቃል
 • ስለ አደጋው ለሚመለከተው የፀጥታ አካል/ፖሊስ ሪፖርትና ክትትል ማድረግ ይጠበቅበታል
 • ደንበኛው አደጋ የደረሰበትን ንብረት የመጠበቅ ኃላፊነት አለበት
 • ደንበኛው ማናቸውንም ዓይነት መረጃዎች ለድርጅቱ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ በተጨማሪም አስፈላጊ የሆኑ ትብብሮችን እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡

ውልን ስለማቋረጥ

 • ደንበኛው በማንኛውም ጊዜ ውሉን ማቋረጥ ሲችል ድርጅቱ ደግሞ የ30 ቀናት የቅድመ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ውሉን ማቋረጥ ይችላል፡፡

ማሳሰቢያ፡- ይህ ፅሑፍ ስለ ዋስትናው አይነት ማብራሪያ ለመስጠት የቀረበ እንጂ በሕግ ፊት የሚፀና ውል አይደለም፡፡