የንብረት ዝርፊያ ዋስትና (Burglary & Housebreaking)

ይህ ውል የመድን ገቢው ንብረቶችን ወይም በመድን ገቢው ቤት በአደራ የተቀመጡ ንብረቶችን ኃይልን ተጠቅሞ በመግባት ወይንም በመውጣት ለሚደርስ ዘረፋ ዋስትና ይሰጣል፡፡

 ውሉን ለመፈፀም የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች

 • የንብረቶች/የዕቃዎች ዝርዝር ከነዋጋቸው
 • ንብረቶቹ/ዕቃዎቹ የሚቀመጡበት ቦታ መግለጫ

በውሉ ሽፋን የማያገኙ ክስተቶች/ሁኔታዎች

 • የእሳት ቃጠሎ ወይንም ፍንዳታ በሚከሰትበት ወቅት ወይንም ከተከሰተ በኋላ ለሚያጋጥም ዝርፊያ
 • ከጦርነትና መሰል ነገሮች ጋር ተያያዥነት ባለው ሁኔታ ለሚፈጠር ዝርፊያ
 • ደንበኛው ካለድርጅቱ ፈቃድ ንብረቶቹ የተቀመጡበት ቦታ ላይ መሰረታዊ ለውጥ ካደረገ
 • ለመኖሪያ ቤትነት ብቻ የሚያገለግል መድን የተገባላቸው ዕቃዎች የሚገኙበት ቤት ከ90 ቀናት በላይ ሰው ሳይኖርበት ሲቀር
 • የተለያዩ ዶክመንቶች፣ የሒሳብ መዝገቦች፣ የኮምፒዩተር መረጃዎች፣ የገንዘብ ቼክ፣ ህጋዊ መረጃዎችና የመሳሰሉት ላይ ለሚደርስ ዝርፊያ ዋስትና አይሰጥም፡፡

በውሉ ላይ መጠበቅ ስላለባቸው ሁኔታዎች

 • ደንበኛው ለንብረቶቹ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርበታል
 • ደንበኛው በውሉ ላይ ያሉ ሁኔታዎችን መፈፀም ይኖርታል

የዋስትና ክፍያን በሚመለከት

 • በውል ዘመኑ ውስጥ የሚከፈሉ እያንዳንዳቸው ክፍያዎች ጠቅላላ መድን ከተገባለት የገንዘብ መጠን ላይ ተቀናሽ ይሆናሉ
 • አዲስ የተተካ ዕቃ በሚኖርበት ጊዜ ለዚሁ ተገቢውን ተመጣጣኝ አረቦን በማስከፈል ሽፋን ይሰጠዋል
 • ድርጅቱ ጉዳት የደረሰበትን ንብረት ከአደጋው በፊት ወደነበረበት ቦታ የመመለስ፣ ከአደጋው በፊት ያለውን ዋጋ የመስጠት፣ ወይንም ንብረቱን በተመሳሳይ መልኩ የመተካት አማራጭ ይኖረዋል፡፡
 • በአደጋው ጊዜ የንብረቱ ዋጋ መድን ከተገባለት ዋጋ ከበለጠ ደንበኛው ለልዩነቱ ኃላፊነቱን የሚወስድ ሲሆን የድርጅቱ የኃላፊነት መጠንም ይህንኑ ባገናዘበ መልኩ በተመጣጣኝ ሁኔታ በንፅፅር የሚሰላ ይሆናል፡፡ ይህም በእያንዳንዱ ንብረት ላይ በተናጠል ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

ውልን ስለማቋረጥ

 • ደንበኛው በማንኛውም ጊዜ ውሉን ማቋረጥ ሲችል ድርጅቱ ደግሞ የ30 ቀናት የቅድመ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ውሉን ማቋረጥ ይችላል፡፡

ማሳሰቢያ፡- ይህ ፅሑፍ ስለ ዋስትናው አይነት ማብራሪያ ለመስጠት የቀረበ እንጂ በሕግ ፊት የሚፀና ውል አይደለም፡፡