የገንዘብ ዋስትና (Money)

ይህ ዋስትና ጥሬ ገንዝብ፣ የባንክ ሰነዶች፣ ቼክ፣ የፖስታ ቤት ትዕዛዞች፣ የገንዘብ ማዘዣዎች፣ የቴምብር ቀረጦች፣ ከንግድ ተቋማት ወደ ባንክ በሚወሰዱበት ጊዜ ወይም ከባንክ ወደ ንግድ ተቋማት በሚመለሱበት ጊዜ ለሚደርስ ዘረፋ እንዲሁም በካዝና በተቀመጡበት ቦታ ለሚደርስ ስርቆት/ዘረፋ ዋስትና ይሰጣል፡፡

 

በውሉ የማይሸፈኑ ሁኔታዎች/ነገሮች

 • በማንኛውም ሰራተኛ/መልዕክተኛ ኢ-ተዓማኒነት ምክንያት የሚመጣ ችግርን፤
 • በተለያዩ ስህተቶች ለሚመጣ የገንዘብ ጉድለትና የገንዘብ የመግዛት አቅም መቀነስ፤
 • የገንዘብ ማስቀመጫ ካዝናው ውሉ ላይ ሽፋን ከተሰጠበት ቦታ ውጭ ሆኖ ለሚመጣ ችግር፤
 • በቂ ጥበቃ ባልተደረገበት መኪና ላይ/ውስጥ ለደረሰ ችግር፤
 • ከጦርነትና እና ከመሳሰሉት ጋር በተያያዘ ለሚመጣ ችግር፤

ውል ለመግባት የሚያስፈልጉ ሁኔታዎች

 • ከስራ ቦታ ወደባንክና ከባንክ ወደ ስራ ቦታ የሚጓጓዘውን እንዲሁም በካዝና ውስጥ ያለውን የገንዘብ መጠን እና የጉዞ ድግግሞሽ በወር ወይም በተወሰነ ጊዜ ተለይቶ መጠቀስ አለበት፡፡
 • ስለገንዘብ ማስቀመጫ ካዝናው ዓይነትና የአጠባበቅ ሁኔታ መረጃ መስጠት ያስፈልጋል፡፡

በውሉ መሰረት ተፈፃሚነት ስለሚኖራቸው ሁኔታዎች

 • ደንበኛው ለገንዘቡ ደህንነት ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ አለበት፡፡
 • ደንበኛው ተገቢውን የሒሳብ መዛግብት መያዝና መጠበቅ አለበት፡፡

በአደጋ ጊዜ መደረግ ስለሚገባቸው ሁኔታዎች

 • ደንበኛው ስለአደጋው በፍጥነት ለድርጅቱ በፅሑፍ ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡
 • ደንበኛው ለሚመለከተው የፖሊስ/የፀጥታ አካል ጉዳዩን በማሳወቅ ክትትል ማድረግ ይኖርበታል፡፡
 • ከዚህ በተጨማሪም ማንኛውንም ድርጅቱ የሚጠይቃቸውን መረጃዎችን ማቅረብና ትብብር ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡

ውል ስለማቋረጥ

ደንበኛው በማንኛውም ጊዜ ውሉን ማቋረጥ ሲችል ድርጅቱ ደግሞ የ30 ቀናት የቅድመ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ውሉን ማቋረጥ ይችላል፡፡

ማሳሰቢያ፡- ይህ ፅሑፍ ስለ ዋስትናው አይነት ማብራሪያ ለመስጠት የቀረበ እንጂ በሕግ ፊት የሚፀና ውል አይደለም፡፡