የግል/የቡድን የአደጋ ዋስትና (Personal/Group Accident Insurance)

ይህ ዋስትና ሰፊ የሽፋን ዓይነት ሲሆን በተቀመጠው የውል ዘመን ውስጥ ሰራተኛው ወይም ሽፋን የተገባለት ግለሰብ በስራ ቦታም ይሁን ከስራ ቦታ ውጭ በውጫዊ እና በዓይን በሚታይ አደጋ ሳቢያ የሚደርስ ድንገተኛ የአካል ጉዳት ወይም ሞትን የሚሸፍን ነው፡፡

ውል ለመግባት የሚያስፈልጉ ሁኔታዎች

 • የሰራተኞች ዝርዝር፣ የሥራ ድርሻና

በውሉ ሽፋን የማይሰጣቸው ነገሮች/ሁኔታዎች

በውሉ ሽፋን ከማይሰጣቸው ክስተቶች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡-

 • ጦርነትና ከጦርነት ጋር ተያያዥነት ባላቸው ምክንያቶች በሚመጣ ክስተት
 • በአደን፣ በመኪና ውድድር፣ ሞተር ሳይክል በማሽከርከር እና መሰል ስፖርታዊ ክንውኖች ምክንያት ለሚመጣ ክስተት
 • ራስን ከማጥፋትና መሰል ሙከራዎች፣ በስካርና አደንዛዥ ዕፆች ተፅዕኖ ከአዕምሮ እክል ጋር በተያያዘ ምክንያት ለሚመጣ ጉዳት
 • መድን ገቢው ከዚህ ቀደም በነበረበት የአካል ጉዳት ምክንያት ለሚመጣ ጉዳት
 • ከእርግዝናና ልጅ ከመውለድ ጋር ተያይዞ ለሚመጣ ጉዳት
 • ከመሬት መንቀጥቀጥ፣ እሳተ ገሞራ እና ተመሳሳይ የተፈጥሮ ክስተቶች ጋር በተገናኘ ለሚመጣ ጉዳት ወይንም ሞት

በውሉ መሰረት ተፈፃሚነት ስለሚኖራቸው ሁኔታዎች

በውሉ መሰረት ተፈፃሚነት ከሚኖራቸው ሁኔታዎች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡-

 • ማንኛውም የአረቦን ክፍያ የሰራተኛውን ደመወዝ ያማከለ ሲሆን በውሉ ዓመት መጨረሻ ላይ የተከፈለውን አረቦን መከፈል ከነበረበት አረቦን ጋር በማነፃፀር ልዩነቱ ለደንበኛው ወይም ለድርጅቱ የሚሰጥ ይሆናል
 • ደንበኛው የውሉን ሁኔታዎች የመጠበቅ ግዴታ ይኖርበታል
 • ደንበኛው የአድራሻ የስራ እና መሰል ለውጦች ካደረገ ለድርጅቱ ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡ ይህ ሳይሆን ከቀረ ግን ውሉ ተፈፃሚነቱን ያጣል፡፡

የዋስትና መጠንን በሚመለከት

ድርጅቱ በውሉ መሰረት የሚሸፈን ክስተትን ተከትሎ በ12 ወራት ውስጥ ለሚመጣ፡ -

 • ሞት፡- የ5 ዓመት ደመወዝ
 • ቋሚ የአካል ጉዳት፡ - የ5 ዓመት ደመወዝ ላይ እንደጉዳቱ መጠን በመቶኛ ታሳቢ የሚሆን
 • ጊዜያዊ የአካል ጉዳት፡ - ወርሃዊ ገቢ ይሆንና ከ52 ሳምንት ላልበለጠ ጊዜ ይሰጣል
 • ጊዜያዊ ከፊል የአካል ጉዳት፡- እንደ ጉዳት መጠኑ የወርሃዊ ደመወዙን በመቶኛ ተሰልቶ ከ52 ሳምንት ላልበለጠ ጊዜ ይሰጣል፡፡
 • ለመድኃኒት፣ ለሆስፒታልና መሰል ወጪዎች፡ - በአንድ አደጋ በሰው እስከ ብር 3000 ይሰጣል፡፡

ማስታወሻ፡- ውሉ በተጨማሪ የአረቦን ክፍያ የተፈጥሮ ህመሞችን እንዲሸፍን ሊደረግ ይችላል፡፡ የዋስትና መጠኑም በስምምነት ይወሰናል፡፡

በአደጋ ጊዜ መደረግ ስላለባቸው ሁኔታዎች

 • ደንበኛው በተቻለ ፍጥነት ስለአደጋው ለድርጅቱ በፅሑፍ ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡ ሆኖም ግን ከክስተቱ መፈፀም ጀምሮ ባሉት 3 ወራቶች ላልቀረበ የካሳ ጥያቄ ድርጅቱ ኃላፊነት አይወስድም፡፡
 • መረጃዎች ማለትም የህክምና እና ሞት ከተከሰተ ደግሞ የአስከሬን ምርመራ፣ የፖሊስ ሪፖርትና የሞት ማረጋገጫ ሰነድ ማቅረብ አስፈላጊ ሲሆን ድርጅቱ የሚጠይቃቸውን ተጨማሪ ማስረጃዎችም ማሟላት ያስፈልጋል፡፡

ውል ስለማቋረጥ

 • ደንበኛው በማንኛውም ጊዜ ውሉን ማቋረጥ ሲችል ድርጅቱ ደግሞ የ30 ቀናት የቅድመ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ውሉን ማቋረጥ ይችላል፡፡

ማሳሰቢያ፡- ይህ ፅሑፍ ስለ ዋስትናው አይነት ማብራሪያ ለመስጠት የቀረበ እንጂ በሕግ ፊት የሚፀና ውል አይደለም፡፡