የእምነት ማጉደል ዋስትና ሽፋን (Fidelity Guarantee Insurance)

ይህ ውል ደሞዝ እየተከፈላቸው በመድን ገቢው ድርጅት ስር የሚሰሩ ሰራተኞችና የስራ ኃላፊዎች እምነት በማጉደል ለሚያደርሱት የገንዘብ ማጉደል ዋስትና ይሰጣል፡፡ የዋስትና ሽፋኑ የሰራተኛውን ልምድና ሌሎች ጉዳዮችን ከግምት ውስጥ በማስገባት በውሉ ላይ በተገለፀው መሰረት በስምምነት ይወሰናል፡፡

 

በውሉ ሽፋን የማያገኙ ሁኔታዎች

 በመድን ውሉ ከማይሸፈኑ ሁኔታዎች ውስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል፡-

  • በመድን መግቢያ ቅፁ ላይ በተሞላው መሰረት መድን ገቢው በውሉ ላይ የተጠቀሱትን ሰራተኞች የስራ ግንኙነት፣ የገንዘብ መጠን፣ ጥበቃ፣ ቁጥጥርና መሰል ነገሮችን ሳያደርግ ቀርቶ ለሚከሰት ችግር
  • በውሉ ላይ በስምምነት ካልተጨመረ በቀር የመድን ውሉ ከተጀመረበት ቀን በፊት በተፈፀመ የሰራተኛ ድርጊት ለሚመጣ ውድመት እና ሰራተኛው በማንኛውም ከድርጅቱ ከተለየ ከ3 ወር በኋላ የታወቀ ጉድለት

የካሳ ክፍያና በአደጋ ጊዜ መደረግ ስላለባቸው ሁኔታዎች

  • ማንኛውም በውሉ መሰረት የሚሸፈን ጉድለት ሲገኝ በፍጥነት ለድርጅቱ በፅሑፍ ማሳወቅ ይኖርበታል
  • ችግር በሚደርስበት ጊዜ ደንበኛው ለሚመለከተው የፖሊስ/የፀጥታ አካል ሪፖርት ማድረግ ይጠበቅበታል
  • ማናቸውም ዓይነት የሰራተኛ የዕምነት/ማጭበርበር ሁኔታዎች ሲከሰቱ መድን ገቢው ለድርጅቱ ወዲያው ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡ በዚህም መሰረት ሪፖርት የተደረገባቸው ሰራተኞች የሚያደርሱትን ቀጣይ ችግሮች ድርጅቱ አይሸፍንም፡፡
  • መድን ገቢው ለእያንዳንዱ ሰራተኛ በገባው የዋስትና መጠን መሰረት ድርጅቱ ክፍያ የሚፈፅም ሲሆን ሰራተኛው መድን ገቢው ላይ ያለው ቀሪ ገንዘብ ካለ ወይንም መድን ገቢው ለሰራተኛው ሊሰጠው የሚገባው ገንዘብ ካለ ከካሳ ክፍያው ላይ ተቀናሽ ይሆናል
  • ደንበኛው ተጨማሪ መረጃ ለድርጅቱ እንደአስፈላጊነቱ ማቅረብ ይኖርበታል
  • ደንበኛው አደጋውን ሊሸፍን የሚችል ሌላ የመድን ውል ካለው የድርጅቱ የኃላፊነት መጠን ከሌላው ውል ጋር በንፅፅር ይሆናል፡፡

ውል ስለመሰረዝ

  • ደንበኛው በማንኛውም ጊዜ ውሉን ማቋረጥ ሲችል ድርጅቱ ደግሞ የ30 ቀናት የቅድመ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ውሉን ማቋረጥ ይችላል፡፡

ማሳሰቢያ፡- ይህ ፅሑፍ ስለ ዋስትናው አይነት ማብራሪያ ለመስጠት የቀረበ እንጂ በሕግ ፊት የሚፀና ውል አይደለም፡፡