የጉዞ ዋስትና /Travel Insurance

የጉዞ ዋስትና ማንኛውም ወደ ሸንገንና ሌሎች የአውሮፓ አገሮች በተለያየ ምክንያት የሚሄድ ሰው ሊገዛው የሚገባ የውል አይነት ሲሆን ውሉ ላይ በተጠቀሰው መጠንና ሁኔታ መሰረት፡-

 

  • ላልተጠበቀና ድንገተኛ የህክምና ወጪ ሽፋን
  • የ24 ሰአት የድጋፍ አገልግሎት
  • በህዝብ ትራንስፖርት ላይ ለሚከሰት ድንገተኛ የአካል ጉዳትና ሞት ካሳ
  • በጉዞ ላይ ለሚከሰት የሻንጣና የእቃ መጥፋት ሽፋን
  • በሌላ አገር ለሚከሰት ህጋዊ ተጠያቂነት የተወሰነ ድጋፍ
  • ለጉዞ መሰረዝና ሌሎች መሰል ያልተጠበቁ ክስተቶች የተወሰነ ሽፋን ይሰጣል

 በሸንገን አገሮች ጉዞ ላይ እያሉ ያልተጠበቀ ችግር ሲያጋጥዎ ከእርስዎ የሚጠበቀው ከክፍያ ነፃ የሆነውን ስልክ መደወል ብቻ ነው፡፡

 ማሳሰቢያ፡- ይህ ፅሑፍ ስለ ዋስትናው አይነት ማብራሪያ ለመስጠት የቀረበ እንጂ በሕግ ፊት የሚፀና ውል አይደለም፡፡