የሕይወት እና የጤና ዋስትና/ Life and Health Assurance

የሕይወት ዋስትና  ምንድን ነው

 

የህይወት ዋስትና ማለት አንድ ሰው በህመም (በተፈጥሮ) ወይም በአደጋ ምክንያት ከዚህ ዓለም ሲለይ እንዲሁም በእርጅና ምክንያት ግለሰቡ በሚያስተዳድረው ወይም በሚጦረው ቤተሰብ ወይም ግለሰብ ላይ ተያይዞ ሊከሰት የሚችለዉን ኢኮኖሚያዊ ጫና (የገንዘብ እጥረት ) የሚያቃልል ዋስትና ነው ፡፡ በተጨማሪም ለችግር ጊዜ ከመድረሱም ባለፈ ዋስትና የገባው ግለሰብ በሕይወት እያለ ተጠቃሚ የሚሆንበት የቁጠባ ዘዴም ጭምር ነው፡፡

ዋና ዋና የሕይወት ዋስትና አይነቶች


  1. የተርም (የተወሰነ ጊዜ) የሕይወት ዋስትና

 ይህ የዋስትና አይነት የመድን ሽፋን የገባው ግለሰብ በህመም (በተፈጥሮ) ወይም በአደጋ ምክንያት ከዚህ ዓለም ቢለይ የውሉ ሙሉ ጥቅም ግለሰቡ ቀድሞ በስም ለጠቀሳቸው ወይም ህጋዊ ወራሾች ካሳ ተከፋይ ያደርጋል ፡፡

ይህንን የመድን ሽፋን በግልም ሆነ በቡድን ማግኘት ሲቻል በጣም ዝቅተኛ በሆነ ክፍያ ከፍተኛ የዋስትና ሽፋን ያስገኛል ፡፡

  1. የኢንዶውመንት የሕይወት ዋስትና

ይህ የሕይወት ዋስትና ለተወሰነ ጊዜና የውል ዘመን በህመም (በተፈጥሮ) ወይም በአደጋ ምክንያት ዋስትና የገባው ግለሰብ ከዚህ ዓለም ቢለይ ቀድሞ በስም ለተጠቀሱ ወይም  ለህጋዊ ወራሾች ካሳ ተከፋይ እንዲሆን ያደርጋል ፡፡

 

እንዲሁም የመድን ሽፋን የገባው ግለሰብ በውል ዘመኑ መጨረሻ ላይ በህይወት ካለ ሙሉ ጥቅሙን ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ በአንድ ጊዜ ወይም በተለያየ ጊዜ ክፍያ እነደምርጫው ይወስዳል ፡፡

 

በተጨማሪም ከሁለት አመት ላላነሰ ጊዜ አረቦን በመክፈልና በውሉ ውስጥ በመቆየት በየጊዜው ለሚያጋጥም የገንዘብ ፍላጎት ማቃለያ የሚውል ውሉ ካፈራው ገንዘብ ላይ እስከ 90 በመቶ ድረስ ብድር የስገኛል ፡፡ ይህንን ሽፋን በግልም ሆነ በቡድን ማግኘት ይቻላል ፡፡

  1. የእድሜ ልክ የህይወት ዋስትና (Whole life)

ይህ የሕይወት ዋስትና እስከተወሰነ ጊዜ ድረስ ብቻ አረቦን (premium) በመክፈል እስከ አድሜ ልክ ድረስ የመድን ሽፋን ያስገኛል ማለትም ዋስትና የገባው ግለሰብ በማንኛውም ዕድሜ /ጊዜ ከዚህ ዓለም ቢለይ በስም ለተጠቀሱ ወይም ህጋዊ ወራሾችን ካሳ ተከፋይ ያደርጋል፡፡

  1. ቀሪ የባንክ ዕዳ ማወራረጃ የህይወት ዋስትና (Mortgage Redemption Insurance)

ይህ የዋስትና አይነት ከባንክ ለመኖሪያ ቤት መግዣ/መስርያ ለሚሰጥ ብድር የሚገባ የመድን ሽፋን ሲሆን ከባንኩ የተበደረው ግለሰብ ብድሩን ከፍሎ ሳይጨርስ ከዚህ ዓለም ቢለይ ቀሪ ዕዳውን ለባንኩ በመክፈል ቤቱን ከ ሃራጅ ሽያጭ ነፃ በማድረግ ለቤተሰብ ቋሚ መጠለያ እንዲሆን ያደርጋል፡፡

ከሕይወት ዋስትና ጋር በተደራቢነት የሚሰጡ የመድን ሽፋኖች

  1. የአደጋ ዋስትና ( Comprehensive Accident Indemnity)

ይህ የመድን ሽፋን በተደራቢነት ከህይወት ዋስትና ጋር የሚሰጥ ሲሆን በአደጋ ምክንያት የሚደርስ የአካል ጉዳት ወይም ድንገተኛ መለየትን ታሳቢ አድርጎ ተጨማሪና ተመጣጣኝ ካሳ የሚያስገኝ የመድን ሽፋን ነው፡፡

በተጨማሪም በአደጋ ምክንያት የሚመጣን ድንገተኛ የህክምና ወጪ ቀድሞ በውሉ ላይ እስከተጠቀሰው የገንዘብ ልክ ድረስ ይሸፍናል፡፡

  1. የቀብር ስርዐት ማስፈጸሚያ ዋስትና (pre-need funeral)

ይህ የመድን ሽፋን በዋነኝነት ውል የገባው ግለሰብ ከዚህ ዓለም ሲለይ ተያይዞ የሚመጡ ወጪዎችንና የቀብር ስርዐት ወጪን ይሸፍናል፡፡

how to buy cialis online